ዋቄፈና፣ የኦሮሞ ህዝብ ባህላዊና ሀይማኖታዊ ትውፊት።

የመጀመሪያው ምእራፍ።

በ ሀሰን ሙሀመድሁሴን ተከተበ

ምስል ፩፦ የፃሃፊው ምስል።

በዚህ ምእራፍ የዋቄፈና ሀይማኖታዊ ፍልስፍናን እንቃኛለን።


1.1 ወቄፈና ምንድነው?

መስል ፩፦ በዋቄፈና ስርአት መመሰረት ዋቃን የሚገዛ ሰው።

ዋቄፈና ማለት የኦሮሞ ህዝብ ሀገር በቀል ሃይማኖት ሲሆን ጥንታዊ መሰረት ያለው ለአንድ አምላክ ብቻ አምልኮን የመፈፀሚያ እምነት ነው (ancient indigenous monotheistic religion)°።(1) ወቄፈና የሚለው ቃል ዋቃ ከሚለው ስም የተመዘዘ ሲሆን ዋቃ ማለት ደግሞ በሰማይ ያለው አምላክ ማለት ነው። በዚህም መሰረት ዋቄፈና በሰማይ ላለው ብቸኛ አምላክ (ዋቃ) እራስን አሳልፎ መስጠትና መገዛት ማለት ነው።(2) በወቄፈና እምነት መሰረት አምልኮ በብቸኝነት የሚገባው የሁሉ ፈጣሪ ልእለ አምላክ ለሆነው ለአንዱ ዋቃ (Waaqa Taokkicha) ብቻ ነው።(3) በዚህም መሰረት ከሰማዩ አምላክ ዋቃ በቀር አንድም አካል የመመለክ መብት አይኖረውም ማለት ነው።(4)
በዚህ መሰረት የኦሮሞ ህዝብ እንደሚከተለው ዋቃን (አምላኩን) ያወድሳል፣
“ኦ አስገረመን! ኦ አስገረመን!… በስድስቱ አስገረምከን! ስድስት፣ The hornbill complains without being sick; ተክሎች በጥበብህ ያብባሉ በንተ ፍቃድ ብቻ ያፈራሉ፣ ማንንም ሳይጠይቅ ውሃውም ይሮጣል ባንተ ፍቃድ ብቻ በራሱ ይፈሳል፣ ምድርም በተወሰነለት ምህዋር ያስኬድክ፣ ገነትን ያለ አንዳች ድጋፍ በራስህ አቆምክ፣ በጠፈር (ህዋም) ላይ ከዋክብትን እንደ ሽምብራ የዘራህ ብቸኛው ገዢ አንተ ዋቃ ብቸኛው አምላክ። ይህ ያንተ ተአምር እጅግ ቢገርመን ተነሱ ለአንድዬው ዋቃ የሰማዪ አምላክ የምድሩ ገዢ ሁሉን አስተናባሪ የሁሉ ባልተቤት ሁሉ ካንተ በታች አንተ ከሁሉ በላይ፣ ለተመልካችህ እርቀህ ለሚጠራህ ቀርበህ፣ ያንተን ተአምር ቆጥረን ብንዘረዝር ወዳንተ ልንፀልይ ተነሳን ተማክረን። ኦ አንተ አምላካችን ዋቃ የለሊት ፅልመትን በቀን ብርሃን አሻገርከን ለንተ ምስጋና እንጂ ማማረር አይሆነን። ክበርልን ሁሌም በምስጋናችን ላይ እዝነትህን ስጠን።” ታድያ ይህ ውዳሴና ፀሎት በወቄፈና እምነት ትልቅ ቦታ አለው። )

1.2 የእምነቱ መሰረት።

መስል ፫፦ የእምነቱ አባቶች ቃሉ።

እንደ ዋቄፈና የእምነት መሰረት ዋቃ ብቸኛው የዚህ ዩኒቨርስ ፈጣሪና አስተነባሪ ስለሆነ የሰዉ ልጅ በብቸኝነት ሊገዛውና ሊያመልከው ይገባል። የአምልኮውን መገለጫ ደግሞ አያና በማለት ይጠራል።(6) በዚህ የአምልኮው መገለጫ (በአያና) በኩል የሰው ልጅ ዋቃን የሚያመልክና የሚገናኙበት መንገድ ነው ማለት ነው።[7) የአያና አምልኮ የዋቃ ብቸኛ ፈጣሪነቱን, ሁሉን አዋቂነቱ, ሀያልነቱንና ምንም የማይሳነው፣ ሁሉን ቻይ አምላክነቱን የሚያጥራሩበት የእምነቱ መሰረት ነው።(8) በተጨማሪም ዋቃ በጣም አዛኝና ፍጠረተ አለሙን አፍቃሪ የሆነ አምላክ ነው።.
በዋቄፈና እምነት መሰረት ዋቃ ባለ ብዙ ስም ባለቤት ሲሆን ስሙም በተለያዪ ቋንቋ የሚገለጽ ነው። በዚህም ዋቃ የሚለው መጠሪያ ባለብዙ ስሙ አንዱ አምላክ ማለት ነው። የኦሮሞ ህዝብም ዋቃን “Waaqa Gurraacha Garaa Garbaa Tokkicha Maqaa Dhibbaa!” ሲል እያሞገሰ ይጠረዋል። ትርጉሙም “ሆደ ሰፊው እንደ ባህር አሱ ነው ጥቁሩ ዋቃችን፣ ብቸኛ ሁነህ ባለ መቶ ስም ባለቤት ነህ) እንደማለት ነው። ጥቁሩ ዋቃ የሚለው መጠሪያ ዋቃን የሁሉም ስነፍጥረት አስገኝነቱንና ጥልቅ ሚስጥራዊነቱንና ለስነ ፍጥረቱ የማይገለጥ አልያም እራሱን እንጂ በምንም የማይመሰል መሆኑን ለማስረዳት የሚውል መጠሪያ ነው።(9)
ይቀጥላል…


     📚📖ዋቢ መፅሐፍቶች📖📚
  • 👉1:- የፕሮ መሀመድ ሀሰን፣ “The Oromo & Christian Highland Kingdom. 1300-1700” ገፅ 7-100 ያለው
  • 👉2:- በርትሌይ ላምበርት፦ “Oromo Religion Myths and Rites of the Western Oromo of Ethiopia: An Attempt to Understand.” ገፅ 75-90
  • 👉3፦ Taha T.፦ “Religious Beliefs among the Oromo: Waaqeffannaa, Christianity and Islam in the Context of Ethnic Identity, Citizenship and Integration” በሚልም ርእስ ኢትዮጵያን ጆርናል ኦፍ ስተዲስ ላይ ያለ አርቲክል።

👉 በኦሮሞ የእምነት ፍልስፍና ዙሪያ ጠለቅ ያለ እውቀት ለማግኘት ዋቢ ካረግኳቸው መፅሀፍት በተጨማሪ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መፅሀፍትን ቢያነቡ ይመከራል።📚=
___📚📖📚__

👉1:- De Salviac, Martial. An Ancient People: Great African Nation: the Oromo. Translation from the 1901 original French edition by Ayalew Kanno. Paris, the French Academy, 2005
👉2:- Bartels, Lambert. 1983. Oromo Religion Myths and Rites of the Western Oromo of Ethiopia: An Attempt to Understand. Berlin:
👉3:- Dietrich Reimer Verlag.”Qaallu Institution: A theme in the ancient rock-paintings of Hararqee—implications for social semiosis and history of Ethiopia”. ResearchGate.
👉4:- CSA, (2007) “Summary and Statistical Report of the 2007 Population and Housing Census”, Available http://www.ethiopia.gov.et/English/Information/Pages/RegionalStates.aspx
👉5:- Enrico Cerulli. “The Folk-Literature of the Galla.”. p. 137.
👉6:- Kelbessa., Workineh (2011). Indigenous and modern environmental ethics : a study of the indigenous Oromo environmental ethic and modern issues of environment and development. Council for Research in Values and Philosophy. Washington, D.C.: Council for Research in Values and Philosophy. ISBN 978-1565182530. OCLC 746470735.
👉7:- Ta’a, T. (2012-01-01). “Religious Beliefs among the Oromo: Waaqeffannaa, Christianity and Islam in the Context of Ethnic Identity, Citizenship and Integration”. Ethiopian Journal of the Social Sciences and Humanities. 8 (1): 87–111–111. ISSN 2520-582X.
👉8:- Magarrssa, Gemechu (1993). Knowledge, Identity and the conniving structure: the case of the Oromo in East and Northeast Africa. University of London. pp. 90–110.
👉9:- Kelbessa., Workineh. “Traditional Oromo Attitudes towards the Environment” (PDF). Social Science Research Report Series. 19: 22–32.
👉10:- Hassen, Mohammed (1983). THE OROMO OF ETHIOPIA, 1500-1850 : WITH SPECIAL EMPHASIS ON THE GIBE REGION. University of London: School of Oriental and African Studies

Leave a Comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s